Yezkuni Key Wet (የዝኩኒ ቀይ ወጥ)

Ingredients:

3 መካከለኛ ጭልፋ (300 ግራም) አልፎ፣ አልፎ የተላጠና ፍሬው ወጥቶ የተከተፈ ዝኩኒ
2 መካከለኛ ጭልፋ የ200 ግራም) በወፍራሙ የተገረደፈ ቀይ ሽንኩርት
3 መካከለኛ ጭልፋ (300 ግራም) ተከትፎ የተጠበሰ ድንች
1 የሾርባ ማንኪያ አዋዜ
6 የሾርባ ማንኪያ (00 ሚሊ ሊትር) ዘይት
1 የሻይ ማንኪያ ቁንዶ በርበሬ
2 የሾርባ ማንኪያ የደቀቀ ነጭ ሽንኩርት
4 የተገረደፈ ቃርያ
2 የሻይ ማንኪያ ጨው
Type:
Foods

Directions

1. ቀይ ሽንኩርቱን በውሃ ብቻ ማብሰል፤
2. ዘይት ጨምሮ ሲቁላላ አዋዜ መጨመር፤
3. ሙቅ ውሃ ጠብ እያደረጉ አዋዜውን ማቁላላት፤
4. ዝኩኒውን ጨምሮ እንዳይፈርስ በዝግታ ማማሰል፤
5. ዝኩኒው ከበሰለ በኋላ የተጠበሰውን ድንች መጨመር ማንተክተክ፤
6. ነጭ ሽንኩርቱን መጨመርና እሳቱን ቀንሶ ማብሰል፤
7. ጨው፣ ቁንዶ በርበሬና ቃርያ ጨምሮ በማስተካከል ማውጣት

Directions Video

en_USEnglish