Yequanta Wet (የቋንጣ ወጥ)
Ingredients:
1 ኪሎ ግራም የበሬ፣ የበግ ወይም የፍየል ሥጋ ቋንጣ
2 መካከለኛ ጭልፋ (300 ግራም) በጣም የደቀቀ ቀይ ሽንኩርት
4 የሾርባ ማንኪያ አዋዜ
2 የሾርባ ማንኪያ ርጥብ ቅመም
1 የሾርባ ማንኪያ ጥቁር ቅመም
3 የሾርባ ማንኪያ ለጋ ቅቤ
ግማሽ የሻይ ማንኪያ ምጥን ሽንኩርት
6 የሾርባ ማንኪያ (00 ሚሊ ሊትር) በጠጅ ወይም በውሃ የተበጠበጠ ርጥብ ቅመም
6 የሾርባ ማንኪያ (00 ሚሊ ሜትር) ዘይት
1 የሻይ ማንኪያ መከለሻ
1 የሻይ ማንኪያ ጨው
Type:
Foods

Directions
1.ቀይ ሽንኩርቱን በሙቅ ውሃ ማብሰል፤
2.ምጥን ሽንኩርት ጨምሮ ማቁላላት፤
3.ዘይት መጨመር፤
4.አዋዜውን ለትንሽ ጊዜ ማቁላላት፤
5.ቅቤና ርጥብ ቅመም መጨመር፤
6.ውሃ ሳይበዛ ጠብ እያደረጉ ማዋሃድ፤
7.ቋንጣውን በጣም አድቅቆ መክተፍ ወይም መቆራረጥ፤
8.በተቁላላው ላይ ጨምሮ ማዋሀድና ጥቁር ቅመም አክሎ ትንሽ ማንተክተክ፤
9.በጠጅ ወይም በውሃ የተበጠበጠ ርጥብ ቅመም መጨመር ለትንሽ ጊዜ ማንሰክሰክ፤
10.መከለሻና ጨው አስተካክሎ ማውጣት፡፡