Yequanta Firfir (የቋንጣ ፍርፍር)
Ingredients:
ግማሽ ኪሎ ግራም የተቆራረጠ ቋንጣ
2 መካከለኛ ጭልፋ (300 ግራም) የደቀቀ ቀይ ሽንኩርት
3 የሾርባ ማንኪያ ምጥን ሽሮ
3 የሾርባ ማንኪያ አዋዜ
2 የሾርባ ማንኪያ ርጥብ ቅመም
ግማሽ የሻይ ማንኪያ ጥቁር ቅመም
4 ፍሬው ወጥቶ የተሰነጠቀ ቃርያ
4 የሾርባ ማንኪያ ቅቤ
ግማሽ የሻይ ማንኪያ ምጥን ሽንኩርት
1 የሻይ ማንኪያ ጨው
Type:
Foods

Directions
1. ቀይ ሽንኩርቱን በውሃ ብቻ ማቁላላት፤
2. ምጥን ሽንኩርት ጨምሮ ማቁላላት፤
3. አዋዜ ጨምሮ በደንብ ማቁላላት፤
4. አዋዜውን ከርጥብ ቅመም ጋር ጨምሮ በደንብ ማሸት፤
5. ቅቤ ጨምሮ ትንሽ ሙቅ ውሃ ማድረግ፤
6. ውሃው መጠጥ ሲል ሽሮውን መጨመርና ማፍላት፤
7. ቋንጣውን ጨምሮ መረቅ እንዲኖረው ካደረጉ በኋላ በጥቁር ቅመምና ጨው ማስተካከል፤
8. ስጋው ሲበስል በእንጀራ ፈትፍቶ ላዩ ላይ ቃርያ ጣል፣ ጣል በማድረግ ማቅረብ፡፡