Yequanta Alicha Wet Bedfin Missir (የቋንጣ አልጫ ወጥ በድፍን ምስር)

Ingredients:

5 መካከለኛ ጭልፋ (ግማሽ ኪሎ ግራም) በትልልቁ የተቆራረጠ ቋንጣ
2 የቡና ስኒ (200 ግራም) ተለቅሞ የተቀቀለ ድፍን ምስር
2 መካከለኛ ጭልፋ (200 ግራም ጎረድ፣ ጎረድ የተደረገ ቀይ ሸንኩርት
2 የሾርባ ማንኪያ ርጥብ ቅመም
1 የሾርባ ማንኪያ እርድ
ግማሽ የሾርባ ማንኪያ ነጭ ቅመም
4 ፍሬው ወጥቶ የተሰነጠቀ ቃርያ
2 የሾርባ ማንኪያ ቅቤ
1 የሻይ ማንኪያ ጨው
Type:
Foods

Directions

1.ቀይ ሽንኩርቱን በውሃ ማብሰል፤
2.መጠጥ ሲል በሙቅ ውሃ ማቁላላት፤
3.ቋንጣውን ጨምሮ ማሸት፤
4.ውሃው ሳይበዛ እንዲበስል መተው፤
5.ሥጋው ከበሰለ በኋላ ምስሩን ጨፍለቅ፤ ጨፍለቅ አድርጎ መጨመር፤
6.ርጥብ ቅመምና እርድ ጨምሮ እሳቱን ቀነስ በማስረግ ማንተከተከ፤
7.ውሃው መጠጥ ብሎ መካከለኛ ይዘት ሲኖረው ቅቤ ጨምሮ ማንሰከሰከ፤
8.ቃርያውን ጣል፣ ጣል አድርጎ ጨውና ነጭ ቅመሙን በማስተካከል ማውጣት፤

Directions Video