Yedereke Gomen Beayb (የደረቀ ጎመን በአይብ)

Ingredients:

5 መካከለኛ ጭልፋ (ግማሽ ኪሎ ግራም) ነጭ ያልኮመጠጠ አይብ
3 የሾርባ ማንኪያ ለጋ ቅቤ
ግማሽ ኪሎ ግራም የአበሻ ጎመን (ቅጠሉ ብቻ)
1 የሾርባ ማንኪያ ሚጥሚጣ
1 የሻይ ማንኪያ የተፈጨ ኮረሪማ
1 የሻይ ማንኪያ ጨው
Type:
Foods

Directions

1. ጎመኑን መርጦ እንጀራ ምጣድ ላይ እያገላበጡ ማድረቅ፤
2. በንጹህ ትሪ ፀሐይ ላይ ትንሽ ማቆየት፤
3. አሽቶ እንዲደርቅና እንዲደቅ ማድረግ፤
4. የደቀቀውን ጎመን፣ አይቡን፣ ኮረሪማውን፣ ጨውንና ሚጥሚጣውን ደባልቆ ማሸት፤
5. ከተቀላቀለ በኋላ ቅቤ መጨመርና በደንብ አዋህዶ ለገበታ ማቅረብ፡፡

Directions Video

en_USEnglish