Yecarot Ena Shenkurt Wet(የካሮትና የሽንኩርት ወጥ)

Ingredients:

3 መካከለኛ ጭልፋ (300 ግራም) አጠር ተደርጎ በቀጭኑ የተከተፈ ካሮት
3 መካከለኛ ጭልፋ (300 ግራም) አጠር ተደርጎ በቀጭኑ የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት
4 ፍሬው ወጥቶ የተሰነጠቀ ቃርያ
3 የሻይ ማንኪያ አዋዜ
ግማሽ የሻይ ማንኪያ ምጥን ሽንኩርት
2 የሻይ ማንኪያ ርጥብ ቅመም
1 የቡና ስኒ (100 ግራም) የምስር ክክ
2 የሻይ ማንኪያ ጨው
1 የሻይ ማንኪያ መከለሻ
6 የሾርባ ማንኪያ (100 ሚሊ ሊትር) ዘይት
Type:
Foods

Directions

1. ቀይ ሽንኩርቱን በውሃ ብቻ ማብሰል፤
2. ምጥን ሽንኩርት ጨምሮ ትንሽ ማቁላላት፤
3. ዘይት ጨምሮ እንዳያር በጥንቃቄ ማማሰልና አዋዜ መጨመር፤
4. ሽንኩርቱ ሲበስል ካሮቱን መጨመርና አዋዜ መጨመር፤
5. ውሃ ጠብ እያደረጉ እንዲበስል መተው፤
6. ካሮቱ ሲበስል የምስር ክኩን ከላዩ መነስነስና ለጥቂት ጊዜ ማንተክተክ፤
7. ርጥብ ቅመሙን ጨምሮ ማብሰል፤
8. ጨውና መከለሻውን አስተካክሎ ቃርያውን ጨምሮ ማውጣት፡፡

Directions Video

en_USEnglish