Yebera Tibis Wet (የበሬ ጥብስ ወጥ)
Ingredients:
1 ኪሎ ግራም ጎረድ፤ ጎረድ ተደርጎ በረጅሙ የተቆራረጠ የታላቅ ሥጋ
2 መካከለኛ ጭልፋ (200 ግራም) የተገረደፈ ቀይ ሽንኩርት
3 የሾርባ ማንኪያ አዋዜ
5 የሾርባ ማንኪያ ቅቤ
ግማሽ የሻይ ማንኪያ ጥቁር ቅመም
2 የሾርባ ማንኪያ ርጥብ ቅመም
2 የሻይ ማንኪያ ምጥን ሽንኩርት
2 የሾርባ ማንኪያ ዘይት
6 የሾርባ ማንኪያ (00 ሚሊ ሊትር) በጠጅ ወይም በውሃ የተበጠበጠ ርጥብ ቅመም
1 የሻይ ማንኪያ መከለሻ
2 የሻይ ማንኪያ ጨው
Type:
Foods

Directions
1.ቀይ ሽንኩርቱን በውሃ ብቻ ማቁላላት፤
2.ምጥን ሽንኩርት ጨምሮ ውሃ ጠብ እያደረጉ ማብሰል፤
3.ሽንኩርቱ እንዳያር ወይም አዋዜ ሲጨመር እያረረ እንዳያስቸግር ዘይት መጨመር፤
4.አዋዜውን ጨምሮ በደንብ መቁላላት፤
5.ሥጋውን መጥበስ ወይም ብረት ምጣድ ላይ በደንብ ጠብሶ ከነውሃው መጨመር፤
6.ውሃ ሳይጨምሩ ርጥብ ቅመምና ጥቁር ቅመም ጨምሮ በደንብ ማብሰል፤
7.ቅቤ መጨመርና አረፋ እንዳይኖረው ማንተከተከ፤
8.እሳቱን ዝቅ አድርጎ በጠጅ ወይም በውሃ የተበጠበጠውን ርጥብ ቅመም መጨመርና ለ0 ደቂቃ ማንተክተክ፤
9.መከለሻውንና ጨውን አስተካክሎ ማውጣት፡፡