Yebera Alicha Minchet Absh (የበሬ አልጫ ምንቸት አብሽ)
Ingredients:
ግማሽ ኪሎ ግራም የተፈጨ ቀይ ሥጋ
2 መካከለኛ ጭልፋ (300 ግራም) የደቀቀ ቀይ ሽንኩርት
1 መካከለኛ ጭልፋ (50 ግራም) የደቀቀ የባሮ ሽንኩርት
2 የሾርባ ማንኪያ እርድ
4 ፍሬው ወጥቶ የተሰነጠቀ ቃርያ
3 ሾርባ ማንኪያ ርጥብ ቅመም
3 የሻይ ማንኪያ ነጭ ቅመም
4 የሾርባ ማንኪያ ቅቤ
2 የሻይ ማንኪያ ጨው
Type:
Foods

Directions
1.ቀይ ሽንኩርቱንና ባሮ ሽንኩርቱን ውሃ ጠብ እያደረጉ ማቁላላት፤
2.መጠጥ ሲል ሥጋውን መጨመር፤
3.ትንሽ ውሃ እያደረጉ በጣም ማሸት፤
4.በደንብ ታሽቶ ሲበስል ቅቤውንና ርጥብ ቅመሙን ጨምሮ እንዲበስልb መተው፤
5.ሲበስል ነጭ ቅመምና እርድ መጨምር፤
6.መጠጥ ሲል ጨው ጨምሮ ሲስተካከል ቃርያውን ጣል፣ ጣል አድርጎ ማውጣት፡፡