Yebeg Zilzil Alicha Wet (የበግ ዝልዝል አልጫ ወጥ)
Ingredients:
1 ኪሎ ግራም ተኩል የበግ ሥጋ ከፍርምባና ከጎድን አጥንት ጋር
5 መካከለኛ ጭልፋ (ግማሽ ኪሎ ግራም) የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት
2 የሾርባ ማንኪያ ርጥብ ቅመም
6 የሾርባ ማንኪያ (00 ሚሊ ሊትር) በጠጅ ወይም በውሃ የተበጠበጠ ርጥብ ቅመም
4 ፍሬው ወጥቶ የተሰነጠቀ ቃሪያ
4 የሾርባ ማንኪያ (00 ግራም) ለጋ ቅቤ
2 የሾርባ ማንኪያ እርድ
ግማሽ የሻይ ማንኪያ ጨው የ ቀለም
1 የሻይ ማንኪያ ነጭ ቅመም
Type:
Foods

Directions
1.ሥጋውን በትንሽ፣ በትንሹ እየዘለዘሉ ማስተካከል፤
2.ሽንኩርቱ እንዳይጠቁር በውሃ ብቻ ማቁላላት፤
3.ውሃው መጠጥ ሲል ሥጋውን ለብ ባለ ውሃ ካጠቡ በኋላ ድስቱ ውስጥ መጨመር፤
4.አልፎ አልፎ እያማሰሉ ቅቤ ጨምሮ እንዲበስል መተው፤
5.ርጥብ ቅመም መጨመርና እንዲበስል መተው፤
6.ሲበስል ውሃውን አስተካክሎ በጠጅ ወይም በውሃ የተበጠበጠውን ርጥብ ቅመም አጥልሎ መጨመር፤
7.እርድ መጨመር፤
8.በነጭ ቅመም አስተካክሎና ጨውን ጨምሮ ቃሪያ ጣል፣ ጣል አድርጎ ማውጣት፡፡