Yebeg Siga Kikil Alicha Wet(የበግ ሥጋ ቅልቅል አልጫ ወጥ)

Ingredients:

2 የበግ ኩላሊት በቁመቱ የተቆራረጠ፣ 1 መካከለኛ ጭልፋ (50 ግራም) ጉበት በቁመቱ የተቆራረጠና 2 መካከለኛ ጭልፋ (300 ግራም) ታጥቦ የተገነፈለና በቁመቱ የተቆራረጠ የበግ ጨጓራ
6 የሾባ ማንኪያ (1oo ሚሊ ሊትር) በጠጅ ወይም በውሃ የተበጠበጠ ርጥብ ቅመም
2 የሾርባ ማንኪያ ርጥብ ቅመም
2 የሾርባ ማንኪያ ቅቤ
4 ፍሬው ወጥቶ የተሰነጠቀ ቃርያ
2 መካከለኛ ጭልፋ (200 ግራም) በቁመቱ የተቆራረጠ ቀይ ሽንኩርት
ግማሽ የሻይ ማንኪያ እርድ
1 የሻይ ማንኪያ ነጭ ቅመም
1 የሻይ ማንኪያ ጨው
Type:
Foods

Directions

1.ቀይ ሽንኩርቱን በትንሽ ውሃ በነጩ ማብሰል፤
2.ርጥብ ቅመምና ቅቤ ጨምሮ በደንብ ማቁላላት፤
3.ቅልቅል ሥጋውን ለብቻው መጥበሻ ላይ አመስ፣ አመስ አድርጎ ቁሌቱ ላይ መጨመርና ማንተክተክ፤
4.በጠጅ ወይም በውሃ የተበጠበጠውን ርጥብ ቅመም መጨመር፤
5.መጠጥ ሲል እርድ ጨምሮ እንዲበስል መተው፤
6.መጠነኛ ውሃ እንዲኖረው ማስተካከል፤
7.ነጭ ቅመም፣ ጨውና ቃርያ ጨምሮ ትንሽ አንተክትኮ ማውጣት፡፡

Directions Video