Yebeg Lega Tibis (የበግ ለጋ ጥብስ)
Ingredients:
ግማሽ ኪሎ ግራም የበግ የሽንጥ ሥጋና የጎድን አጥንት
2 መካከለኛ ጭልፋ (200 ግራም) የተገረደፈ ቀይ ሽንኩርት
4 ፍሬው ወጥቶ የተገረደፈ ቃርያ
2 የሾርባ ማንኪያ ለጋ ቅቤ
1 የሻይ ማንኪያ ነጭ ቅመም
1 የሻይ ማንኪያ ጨው
Type:
Foods

Directions
1.ሥጋውን ረዘም አድርጎ መቆራረጥ፣
2.የጎድን አጥንቱን ሶስት ቦታ መቆራረጥ፣
3.በመጠኑ የጋለ መጥበሻ ወይም ምጣድ ላይ ቅቤ መጨመር፣
4.የተቆራረጠውን ሥጋና አጥንት መጥበሻው ወይም ምጣዱ ላይ መጨመር፤
5.እንዳይገነትር ቶሎ፣ ቶሎ ማገላበጥ፤
6.ሥጋው በከፊል ከበሰለ በኋላ ሽንኩርቱንና ቃሪያውን መጨመር፣
7.ነጭ ቅመሙንና ጨውን አስተካክሎ ማውጣት፡፡