Yebeg Alicha Wet (የበግ አልጫ ወጥ)

Ingredients:

2 ኪሎ ግራም የበግ ሥጋ ከነአጥንቱ
5 መካከለኛ ጭልፋ (ግማሽ ኪሎ ግራም) የተገረደፈ ቀይ ሽንኩርት
2 መካከለኛ ጭልፋ (200 ግራም) የተገረደፈ ባሮ ሽንኩርት
4 ፍሬው ወጥቶ በወፍራሙ የተከተፈ ቃሪያ
3 የሾርባ ማንኪያ ለጋ ቅቤ
2 የሾባ ማንኪያ ነጭ ቅመም
1 የሾርባ ማንኪያ ርጥብ ቅመም
3 የሾባ ማንኪያ በጠጅ ወይም በውሃ የተበጠበጠ ርጥብ ቅመም
1 የሾርባ ማንኪያ እርድ
1 የሻይ ማንኪያ ጨው
Type:
Foods

Directions

1.ሥጋውንና አጥንቱን በትንንሹ መቆራረጥ፤
2. ሽንኩርቱንና ባሮውን በውሃ ብቻ ማቁላላት፤
3.ውሃው መጠጥ ሲል ሥጋውን ጨምሮ በነጩ እያማሰሉ ሳይቀላ በወፍራሙ ማብሰል፤
4.ሙቅ ውሃ ጠብ እያደረጉ ቅቤና ርጥቡን ቅመም ጨምሮ ማብሰል
5.እርድ መጨመር፤
6.ሲበስል በጠጅ ወይም በውሃ የተበጠበጠውን ርጥብ ቅመም አጥልሎ ጨምሮ እሳቱን ዝቅ አድርጎ ለትንሽ ጊዜ ማንተከተከ፤
7.ነጭ ቅመሙንና ጨውን አስተካክሎ ቃሪያ ጣል፣ ጣል አድርጎ ማውጣት፣
8.ሳይፈተፍቱ ማቅረብ፡፡

Directions Video

en_USEnglish