Yeatkilt Key Wet (የአትክልት ቀይ ወጥ)
Ingredients:
3 መካከለኛ ጭልፋ (300 ግራም) የተገረደፈ ካሮት
3 መካከለኛ ጭልፋ (300 ግራም) የተገረደፈ ድንች
3 መካከለኛ ጭልፋ (300 ግራም) የተገረደፈ ፎሶሊያ
3 መካከለኛ ጭልፋ (300 ግራም) የተገረደፈ ቀይ ሽንኩርት
3 የሾርባ ማንኪያ አዋዜ
2 የሾርባ ማንኪያ ርጥብ ቅመም
ግማሽ የሻይ ማንኪያ ምጥን ሽንኩርት
ግማሽ የሻይ ማንኪያ ጥቁር ቅመም
2 የሻይ ማንኪያ ጨው
6 የሾርባ ማንኪያ (oo ሚሊ ሊትር) ዘይት
Type:
Foods

Directions
1. ቀይ ሽንኩርቱን በዘይት ማቁላላት፤
2. ሽንኩርቱ ሲበስል ምጥን ሽንኩርት መጨመርና እንደገና ማቁላላት፤
3. በደንብ ከተዋሀደ በኋላ አዋዜ መጨመርና ሙቅ ውሃ ጠብ እያደረጉ ማብሰል፤
4. ካሮቱን ጨምሮ በደረቁ ማቁላላት፤
5. ፎሶሊያ መጨመርና በደረቁ ማብሰል፤
6. ርጥብ ቅመምና ትንሽ ውሃ ጨምሮ እንዲበስል መተው፤
7. ካሮቱና ፎሶሊያው ሲበስል ድንቹን ጨምሮ እንዳይፈርስ በጥንቃቄ ማማሰል፤
8. እሳቱን ቀንሶ በዝግታ ማንተክተክ፤
9. መረቁ እንዳይበዛ አስተካክሎ ጥቁር ቅመም በመጨመር ማንሰክሰክ፤
10. ጨው ጨምሮ አስተካክሎ ማውጣት፡፡