Yeatkilt Alicha Wet (የአትክልት አልጫ ወጥ)
Ingredients:
3 መካከለኛ ጭልፋ (300 ግራም) በረጅሙ የተከተፈ ካሮት
3 መካከለኛ ጭልፋ (300 ግራም) በረጅሙ የተከተፈ ፎሶሲያ
3 መካከለኛ ጭልፋ (300 ግራም) በረጅሙ የተከተፈ ድንች
3 መካከለኛ ጭልፋ (100 ግራም) በረጅሙ የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት
1 መካከለኛ ጭልፋ (00 ግራም) በረጅሙ የተከተፈ ነጭ ሽንኩርት
4 ፍሬው ወጥቶ የተገረደፈ ቃርያ
2 የሻይ ማንኪያ ጨው
3 የሾርባ ማንኪያ ርጥብ ቅመም
2 የሾርባ ማንኪያ ነጭ ቅመም
6 የሾርባ ማንኪያ (oo ሚሊ ሊትር) ዘይት
2 የሻይ ማንኪያ እርድ
Type:
Foods

Directions
1. ቀይ ሽንኩርቱን በውሃ ብቻ በነጩ ማብሰል፤
2. ዘይት ጨምሮ ሽንኩርቱን ማብሰል፤
3. ሽንኩርቱ በሰል ሲል ካሮትና ፎሶሊያ መጨመርና በደረቁ ማቁላላት፣
4. ትንሽ ሙቅ ውሃ ጠብ እያደረጉ ማብሰል፤
5. መረቁ ሳይበዛ እንዲበስል መተውና አልፎ፣ አልፎ በዝግታ ማማሰል፣
6. ካሮቱና ፎሶሊያው ሲበስል ድንች፣ ርጥብ ቅመምና ነጭ ሽንኩርት ጨምሮ ትንሽ ውሃ አድርጎ መተው፤
7. መጠጥ ሲል እርድ፣ ጨውና ነጭ ቅመም ጨምሮ ማንተክተክ
8. ቃርያውን ጨምሮ አስተካክሎ ማውጣት፡፡