Ye Abish Dukat (የአብሽ ዱቄት (የትግራይ ድቁስ))

Ingredients:

3 የቡና ስኒ (ግማሽ ኪሎ ግራም) አብሽ
10 የቡና ስኒ ጥሬ ጨው
ሩብ ኪሎ ግራም ፍሬው ወጥቶ ጎረድ ጎረድ የተደረገ ርጥብ የአበሻ ቃርያ
1 የቡና ስኒ ደረቅ በሶብላ
Type:
Foods

Directions

1.አብሹን በደንብ ለቅሞ በእጅ ሳይነኩ ማጠብና እንዲደርቅ ማድረግ፤
2.ቃርያውንና በሶብላውን ለቅሞ ከጨው ጋር መደለዝ፤
3.እንዲደርቅ የማያጣብቅ እቃ ላይ ማስጣት
4.አብሹን ወርቃማ መልክ እስኪያመጣ መቁላት፤
5.ከተደለዘው ጋር በመቀላቀል እንዲልም መፍጨት ወይም በንፁህ ሙቀጫ መውቀጥ፤
6.በጠቅጣቃ ወንፊት መንፋት፡፡


በዚህ መልኩ የተዘጋጀ የአብሽ ዱቄት ባብዛኛው እንጀራ ላይ በስሱ ተነስንሶ ይበላል፡፡

Directions Video