Nech Shiro (ነጭ ሽሮ)

Ingredients:

6 ኪሎ ግራም የአተር ክክ
3 ኪሎ ግራም የባቄላ ክክ
1 ኪሎ ግራም ቀይ ሽንኩርት
1 ኪሎ ግራም ነጭ ሽንኩርት
ግማሽ ኪሎ ግራም ዝንጅብል
1 የቡና ስኒ ድንብላል
1 የቡና ስኒ በሶብላ
1 የቡና ስኒ ነጭ አዝሙድ
1 የቡና ስኒ ጤና አዳም
1 የቡና ስኒ የተፈለፈለ ኮረሪማ
2 የቡና ስኒ ጨው
Type:
Foods

Directions

1.የባቄላውንና የአተሩን ክክ በደንብ አጥቦ መቀላቀል፤
2.ቀይ ሽንኩርቱን፣ ነጭ ሽንኩርቱን፣ ዝንጅብሉንና ጤና አዳሙን ለየብቻ ልጦና አጥቦ ገርደፍ፣ ገርደፍ ማድረግ፤
3.ከተቀላቀለው ክክ ግማሹን ወስዶ ከተገረደፈው ጋር ደባልቆ መውቀጥ፤
4.የቀረውን ክክ ቀላቅሎ ለአንድ ቀን በላስቲክ መዘፍዘፊያ ሳፋ አፍኖ ማሳደር፤
5.በቀጣዩ ቀን የማያጣብቅ እቃ ላይ ማስጣትና ከሁለት እስከ ሶስት ቀን እንዲደርቅ መተው፤
6.ድንብላሉን፣ በሶብላውን፣ ነጭ አዝሙዱን፣ ኮረሪማውን ጨውን ለየብቻ ማመስ፤
7.ሁሉንም ቀላቅሎ ማስፈጨትና በጠቅጣቃ ወንፊት ነፍቶ ማስቀመጥ፡፡

Directions Video