Mtin Shiro (ምጥን ሽሮ)

Ingredients:

1 ኪሎ ግራም ንፁህ አተር
1 ኪሎ ግራም ንፁህ ሽምብራ
3 ኪሎ ግራም በርበሬ
ግማሽ ኪሎ ግራም የተገረደፈ ነጭ ሽንኩርት
ግማሽ ኪሎ ግራም የተገረደፈ ዝንጅብል
ግማሽ ኪሎ ግራም የተገረደፈ ቀይ ሽንኩርት
ሩብ ኪሎ ግራም የተገረደፈ ጤና አዳም
ሩብ ኪሎ ግራም ድንብላል
ሩብ ኪሎ ግራም ነጭ አዝሙድ
4 የቡና ስኒ (200 ግራም) ደረቅ በሶብላ
10 የቡና ስኒ ጨው
ሩብ ኪሎ ግራም የተፈለፈለ ኮረሪማ
Type:
Foods

Directions

1.አተሩን በመካከለኛ ደረቅ ቆልቶ ውሃ ውስጥ ለአምስት ደቂቃ መዘፍዘፍ፤
2.ሽምብራውን እንዲሁ በመካከለና ደረጃ ቆልቶ ውሃ ውስጥ ለአምስት ደቂቃ መዘፍዘፍ
3.ሰፋ ያ ነገር ላይ ለየብቻ ማስጣት፤
4.እንዲደርቁ እያገላበጡ መልቀም፤
5.ከደረቁ በኋላ ለየብቻ መከካት ወይም ወፍጮ ቤት ወስዶ ለየብቻ ማስከካት፤
6.አተሩንና ሽምብራውን ለየብቻ ለቅሞና አበጥሮ ከገለባው በመለየት ጥቁር፣ ጥቁሩን ግልፋፊ ሙልጭ አድርጎ ማውጣት፤
7.መቀላቀል፤
8.በርበሬውን መልቀም፤
9.ቀይ ሽንኩርቱን፣ ጤና አዳሙን፣ ዝንጅብሉንና ነጭ ሽንኩርቱን ከበርበሬው ጋር ቀላቅሎ ጨው እየጨመሩ በትንሽ፣ በትንሹ በሙቀጫ ደልዞ መዘፍዘፊያ ውስጥ ማድረግ፤
10.ተደልዞ ሲያበቃ የአተሩንና የሽምብራውን ክክ ደባልቆ በላስቲክ ሸፍኖና ደምድሞ ነፋስ በማያስገባ መልኩ ከድኖ ማሳደር፤
11.በቀጣዩ ቀን የማያጣብቅ ማስጫ ላይ ማስጣት፤
12.እየተከታተሉ በደንብ እንዲደርቅ ማድረግ፤
13.ድንብላሉን፣ ነጭ አዝሙዱን፣ በሶብላውንና ኮረሪማውን ማዘጋጀት፤
14.ለማስፈጨት ወደወፍጮ ቤት ሲሄዱ የተዘጋጁትን ቅመሞት (ተራ ቁጥር 13 ላይ የተጠቀሱትን) ለየብቻ ማመስ፤
15.ሁሉንም ከክኩ ጋር ደባቆ ማስፈጨት፤
16.የተፈጨውን በደንብ መንፋት፡፡

Directions Video