Milas Ena Senber (ምላስና ሰንበር ለብለብ)

Ingredients:

1 ኪሎ ግራም ሰንበር (ጨጓራ ያለበት)
1 የበሬ ምላስ
3 መካከለኛ ጭልፋ (300 ግራም) የተገረደፈ ቀይ ሽንኩርት
2 መካከለኛ ጭልፋ በቁመቱ የተቆራረጠ ቃርያ
3 የሾርባ ማንኪያ በቁመቱ የተቆራረጠ ነጭ ሽንኩርት
2 የሾርባ ማንኪያ ቅቤ
3 የሾርባ ማንኪያ ሚጥሚጣ
ግማሽ የሻይ ማንኪያ ነጭ ቅመም
1 የሻይ ማንኪያ ጨው
Type:
Foods

Directions

1.ሰንበሩንና ጨጓራውን ሳይላጥ በቁመቱ መቁረጥ፤
2.ቀይ ሽንኩርቱን መጥበሻው ላይ አድርጎ ማቁላላት፤
3.ቃርያውንና ነጭ ሽንኩርቱን ጨምሮ ትንሽ ማማሰል፤
4.በቁመቱ የተቆረጠውን ምላስ፣ ሰንበርና ጨጓራ ለብቻ በቅቤ አመስ፣ አመስ አድርጎ ቁሌቱ ላይ መጨመር፤
5.ጨው፣ ሚጥሚጣና ነጭ ቅመም ጨምሮ በትኩሱ ለገበታ ማቅረብ፤ ለብለብ ሲደረግ በፍጥነት መሆን አለበት፡፡ ብዙ ከታመሠ ይገነትራል፡፡

Directions Video