Gored Gored (ጎረድ፣ ጎረድ)

Ingredients:

ግማሽ ኪሎ ግራም ጎረድ፣ ጎረድ የተደረገ የታላቅ ሥጋ
3 የሾርባ ማንኪያ አዋዜ
2 የሾርባ ማንኪያ ርጥብ ቅመም
4 የሾርባ ማንኪያ ቅቤ
ግማሽ የሻይ ማንኪያ ጥቁር ቅመም
ግማሽ የሻይ ማንኪያ መከለሻ
1 የሻይ ማንኪያ ጨው
Type:
Foods

Directions

1.አዋዜው እንዳያር በውሃ ብቻ በጥንቃቄ ማቁላላት፤
2.ውሃው መጠጥ ሲል ርጥብ ቅመሙን ጨምሮ ውሃ ጠብ እያደረጉ ማማሰል፤
3.እጅግም በጣም ሳይወፍር፣ እጅግም በጣም ሳይቀጥን ጨው ጨምሮ ማውጣት፤
4.ቀዝቀዝ ሲል ቅቤ፣ መከለሻና ጥቁር ቅመም ጨምሮ ማማሰል፤
5.ጎረድ፣ ጎረድ የተደረገውን ሥጋ እንዳስፈላጊነቱ እየቀነሱ ከተዘጋጀው ማባያ ጋር እየለወሱ ለገበታ ማቅረብ፡፡

Directions Video