Dfin Misir Beayb (ድፍን ምስር በአይብ)

Ingredients:

2 የቡና ስኒ (200 ግራም) በስሎ ጨፍለቅ፣ ጨፍለቅ የተደረገ ድፍን ምስር
2 መካከለኛ ጭልፋ (200 ግራም) ደረቅ አይብ
1 መካከለኛ ጭልፋ (50 ግራም) የደቀቀ ቀይ ሽንኩርት
ግማሽ የሾርባ ማንኪያ ሚጥሚጣ
5 የሾርባ ማንኪያ ዘይት
1 የሾርባ ማንኪያ ርጥብ ቅመም
ግማሽ የሻይ ማንኪያ ጥቁር ቅመም
ግማሽ የሻይ ማንኪያ መከለሻ
ግማሽ የሻይ ማንኪያ ምጥን ሽንኩርት
2 የሻይ ማንኪያ ጨው
Type:
Foods

Directions

1. ቀይ ሽንኩርቱን በውሃና በዘይት ማብሰል፤
2. ምጥን ሽንኩርት ጨምሮ ማቁላላት፤
3. ውሃ ጠብ እያደረጉ ማብሰል፤
4. ርጥብ ቅመም መጨመርና ትንሽ ማማሰል፤
5. ምስሩን ጨምሮ መረቅ እንዳይኖረው እየተጠነቀቁ በደረቁ ማብሰል፤
6. ጥቁር ቅመምና ውሃ ጠብ እያደረጉ ማንተክተክ፤
7. መከለሻና ጨው ጨምሮ ደረቅ አድርጎ አስተካክሎ ማውጣት፤
8. አይቡን ፈርፍሮ በሚጥሚጣ ማሸት፤
9. ወጡ ሲቀዘቅዝ ከአይቡ ጋር ቀላቅሎ ለገበታ ማቅረብ፡፡

Directions Video

en_USEnglish