Derek Tej (ደረቅ ጠጅ)
Ingredients:
1 ጆግ ወፍራም የጠጅ ማር
3 ጆግ ውሃ
ግማሽ ጆግ (200 ግራም) የጌሾ ቅጠል
1 የሻይ ማንኪያ በርበሬ
Type:
Drinks

Directions
1.በደንብ በታጠበና በታጠነ እቃ ውስጥ ማሩን በውሃ በጥብጦና አጥልሎ ማስቀመጥ
2.በአራተኛው ቀን ሲፈላ ጌሾውን በአንድ ጆግ ውሃ ለስስ ያለ እሳት ላይ ጥዶ ማንተክተክ፤
3.ከእሳት አውርዶ ትንሽ ቀዝቀዝ ሲል ከተበጠበጠው ማር ጋር ደባልቆ እንዲፈላ ከድኖ ማስቀመጥ፤
4 በአራተኛው ቀን ማጥለልና ጌሾውን ማስወገድ፤
5. በርበሬ የታጠነ እቃ ውስጥ ማስቀመጥ፤
6. ሲፈላ መጠቀም፡፡
በዚህ መልኩ በተዘጋጀ ጠጅ እስከ አንድ ወር ድረስ መጠቀም ይቻላል፡፡