Berbera (በርበሬ)
Ingredients:
20 ኪሎ ግራም በርበሬ
3 ኪሎ ግራም ነጭ ሽንኩርት
2 ኪሎ ግራም ዝንጅብል
ግማሽ ኪሎ ግራም በሶብላ
ግማሽ ኪሎ ግራም ድንብላል
ግማሽ ኪሎ ግራም ነጭ አዝሙድ
5 የቡና ስኒ (ሩብ ኪሎ ግራም) ጥቁር አዝሙድ
1 ኪሎ ግራም ጨው
1 ኪሎ ግራም በደንብ ተወቅሎ የደረቀ አብሽ
ሩብ ኪሎ ግራም ጤና አዳም
1 ኪሎ ግራም ኮረሪማ
2 ኪሎ ግራም ቀይ ሽንኩርት
ግማሽ ኪሎ ግራም ጎመን ዘር ወይም ኑግ
Type:
Foods

Directions
1.ሶስት ሳፋዎች ውሃ ሞልቶ ማዘጋት፤
2.አንደኛው ሳፋ ውስጥ በርበሬውን ጨምሮ በወንፊት እያጠነፈፉ አውጥቶ ሁለተኛው ሳፋ ላይ መጨመር፤
3.ሶስተኛው ሳፋ ውስጥ ንፁህ ውሃ ሞልቶ በርበሬውን ማለቅለቅ፤
4.በወንፊት እያጠነፈፉ ውሃ ሊያሳልፍ በሚችል ንፁህ ማስጫ ላይ ማስጣት፤
5.በርበሬውን መቀንጠስ፤
6.በርበሬው ከደረቀ በኋላ መደለዝ፣ ማለትም በጤና አዳም፣ ከዝንጅብል፣ ከነጭ ሽንኩርትና ከቀይ ሽንኩርት ጋር ደልዞ ግጥም የሚል እቃ ውስጥ ማሳደር፤
7.በቀጣዩ ቀን ብትን አድርቶ የማያጣብቅ እቃ ላይ ማስጣት፣
8.በእንጨት እያማሰሉ ማድረቅ፤
9.ደረቅ ቅመሞቹን (በሶብላውን፣ ድንብላሉን፣ ነጭ አዝሙዱን፣ ጥቁር አዝሙዱን፣ አብሹን፣ ኮረሪማውን፣ ጎመን ዘሩን) እና ጨውን በየተራ ለየብቻ በደንብ ማመስ፤
10.ሁሉም ቀላቅሎ ማስፈጨት፡፡
(እዚህ ላይ አብሹ በጣም መብሰል እንዳለበት መገንዘብ ያስፈልጋ፡፡ ጎመን ዘር
ወይም ኑግ የሚጨመረውም ቅባትነት ስላለው ሲቀመጥ እንዳይበላሽና ለስለስ
ያለ ጣዕም እንዲኖረው ነው፡፡)