Yetefeche Yebeg Engocha Wet (የተፈጨ የበግ እንጎቻ ወጥ)
Ingredients:
2 መካከለኛ ጭልፋ (300 ግራም) በደቃቁ የተፈጨ ቀይ የበግ ስጋ
2 የቡና ስኒ (100 ግራም) የፉርኖ ዱቄት
5 እንቁላል (ነጩን ብቻ)
2 መካከለኛ ጭልፋ (300 ግራም) የደቀቀ ቀይ ሽንኩርት
3 የሾርባ ማንኪያ አዋዜ
1 የሾርባ ማንኪያ ርጥብ ቅመም
1 የሾርባ ማንኪያ (00 ሚሊ ሊትር) በጠጅ ወይም በውሃ የተበጠበጠ ርጥብ ቅመም
1 የሻይ ማንኪያ ምጥን ሽንኩርት
2 የሾርባ ማንኪያ የተፈጨ ቅርንፉድ
1 የሻይ ማንኪያ የተፈጨ ኮረሪማ
ግማሽ ሊትር ዘይት
2 የሾርባ ማንኪያ ቅቤ
1 የሻይ ማንኪያ ጥቁር ቅመም
1 የሻይ ማንኪያ ጨው
Type:
Foods

Directions
1.የበጉን ሥጋ፣ የፉርኖ ዱቄት፣ ኮረሪማ፣ ቅርንፉድና የእንቁላል ነጩን ክፍል ብቻ ደባልቆ በደንብ ማሸት፤
2.አድበልብሎ እንደ እንጎቻ መፍጠፍ፤
3.ስድስት የሾርባ ማንኪያ ዘይት አስቀርቶ በሌላው ዘይት እሳት በጣም ሳይገባ መጥበስ፤
4.ከተጠበሰ በኋላ ለብቻ ማስቀመጥ፤
5.ቀይ ሽንኩርቱን፣ ትንሽ ውሃና ምጥን ሽንኩርቱን ጨምሮ ውሃ እስኪመጥ ድረስ ማቁላላት፤
6. ውሃው ሲመጥ ድርቅ እንዳይል ያስቀሩትን ስድስት የሾርባ ማንኪያ ዘይት ጨምሮ ማቁላላት፤
7.አዋዜና ቅቤ ጨምሮ ለትንሽ ጊዜ ካማሰሉ በኋላ ጥቁር ቅመምና ርጥብ ቅመሙን ጨምሮ ማንተክተክ፤
8.እንደተንተከተከ ጨውን ካስተካከሉ በኋላ ትንሽ ውሃ አድርጎ ሊወጣ ሲል የተጠበሰውን የበግ እንጎቻ መከተት፤
9.በጠጅ ወይም በውሃ የተበጠበጠውን ርጥብ ቅመም ጨምሮ ትንሽ ማንሰክሰክና ማውጣት፡፡