Yequanta Wet Bebekele Bakala (የቋንጣ ወጥ በበቀለ ባቄላ)

Ingredients:

ግማሽ ኪሎ ግራም በረጅሙ የተዘለዘለ ቋንጣ
3 የቡና ስኒ (300 ግራም) በቅሎ የተፈለፈለ ባቄላ
2 መካከለኛ ጭልፋ (200 ግራም) በረጅሙ የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት
1 እግር ርጥብ በሶብላ
2 የሾርባ ማንኪያ ርጥብ ቅመም
1 የሾርባ ማንኪያ እርድ
2 የሾርባ ማንኪያ በረጅሙ የተከተፈ ነጭ ሽንኩርት
4 የሾርባ ማንኪያ ቅቤ
2 የሻይ ማንኪያ ነጭ ቅመም
1 የሻይ ማንኪያ ጨው
4 ፍሬው ወጥቶ የተሰነጠቀ ቃርያ
Type:
Foods

Directions

1. ቀይ ሽንኩርቱን በውሃ ብቻ ማብሰል፤
2. ባቄላውን በላዩ መጨመር፤
3. እርድ ጨምሮ ብዙ ሳያቁላሉ እንዲበስል መተው፤
4. ብዙ ሳይበስል ቋንጣውንና ነጭ ሽንኩርቱን ጨምሮ ማንተክተክ፤
5. ርጥቡን ቅመም ጨምሮ ለሰስ ባለ እሳት ማብሰል፤
6. ቅቤ ጨምሮ በመካከለኛ ይዘት ማንሰክሰክ፤
7. ነጭ ቅመምና ጨው አስተካክሎ፣ ቃርያና በሶብላውን ጣል አድርጎ ማውጣት፡፡

Directions Video

amAmharic