Yequanta Shiro Wet (የቋንጣ ሽሮ ወጥ)

Ingredients:

ግማሽ ኪሎ ግራም የተወቀጠና የላመ ቋንጣ
2 መካከለኛ ጭልፋ (300 ግራም) የደቀቀ ቀይ ሽንኩርት
3 የሾርባ ማንኪያ አዋዜ
ግማሽ የሻይ ማንኪያ ምጥን ሽንኩርት
3 የሾርባ ማንኪያ ቅቤ
6 የሾርባ ማንኪያ (100 ሚሊ ሊትር) በጠጅ ወይም በውሃ የተበጠበጠ ርጥብ ቅመም
1 የሻይ ማንኪያ ጥቁር ቅመም
1 የሻይ ማንኪያ መከለሻ
1 የሻይ ማንኪያ ጨው
3 የሾርባ ማንኪያ ዘይት
Type:
Foods

Directions

1.ቀይ ሽንኩርቱን በውሃ ብቻ ማቁላላት፤
2.ምጥን ሽንኩርት መጨመር፤
3.ሽንኩርቱ ውሃ እስኪመጥ ማቁላላት፤
4.ዘይት መጨመር፤
5.አዋዜውን ጨምሮ በደንብ ማቁላላት፤
6.አዋዜው በደንብ ከተቁላላ በኋላ ጥቁር ቅመም፣ ቅቤና በጠጅ ወይም በውሃ የተበጠበጠውን ርጥብ ቅመም ጨምሮ ማንተክተክ፤
7.የተወቀጠውን ቋንጣ እንደ ሽሮ መነስነስና በዝግታ ማማሰል፤
8.ለትንሽ ጊዜ ውሃውን አጠር አድርጎ ካንተከተኩ በኋላ ጨውና መከለሻውን አስተካክሎ ማውጣት፡፡

Directions Video

amAmharic