Yedoro Michet Abish (የዶሮ ምንቸት አብሽ)

Ingredients:

የ መካከለኛ ዶሮ ዋና፣ ዋና ብልቶች
6 የሾርባ ማንኪያ (100 ሚሊ ሊትር) ደረቅ ጠጅ ወይም ግማሽ ጆግ የቀረረ እርሾ (መዘፍዘፊያ)
2 መካከለና ጭልፋ(300 ግራም) የደቀቀ ቀይ ሽንኩርት
3 የሾርባ ማንኪያ አዋዜ
3 የሾርባ ማንኪያ ዘይት
6 የሾርባ ማንኪያ (100 ሚሊ ሊትር) በጠጅ ወይም በውሃ የተበጠበጠ ርጥብ ቅመም
5 የሾርባ ማንኪያ ቅቤ
ግማሽ የሻይ ማንኪያ ምጥን ሽንኩርት
1 እግር ርጥብ በሶብላ
3 የሾርባ ማንኪያ ርጥብ ቅምም
1 የሻይ ማንኪያ መከለሻ
1 የሻይ ማንኪያ ጨው
Type:
Foods

Directions

1. ዋና ዋና ብልቶቹን በውሃ ማጠብ፣ ደረቅ ጠጅ ወይም እርሾው ውስጥ ለሩብ ሠዓት መዘፍዘፍ፣ እንደገና በውሃ አፅድቶ ብልቶቹን አስተካክሎ ማስቀመጥ፤
2. ቀይ ሽንኩርቱን በራሱ ውሃ ብቻ ማብሰል፤
3. ምጥን ሽንኩርት ጨምሮ በደንብ ማቁላላት፤
4. ሽንኩርቱን ምጥን ሽንኩርት በደንብ ሲቁላላ ዘይት ጨምሮ ትንሽ ማማሰል፤
5. አዋዜ መጨመርና ትንሽ ውሃ ጠብ እያደረጉ ማሸት (አዋዜውን በሚቁላላበት ጊዜ ውሃ ጠብ እያደረጉ የድስቱን ዳር ዳር መቆጣጠር)
6. አዋዜው ከተቁላላ በኋላ የተከተፈውን የዶሮ ሥጋ መጨመር ውሃ ሳይጨምሩ እስኪመጥ ድረስ ማብሰል፤
7. ቅቤና ርጥብ ቅመም ጨምሮ በደንብ ማብሰል፤
8. በስሎ ውሃውን ሲጨርስ በጠጅ ወይም በውሃ የተበጠበጠውን ርጥብ ቅመም መጨመርና እሳቱን ዝቅ አድርጎ ማንሰክሰክ፤
9. መከለሻና ጨውን አስተካክሎ ካወጡ በኋላ በሶብላውን ጨምሮ ለገበታ ማቅረብ፡፡

Directions Video

amAmharic