Yedereqe Asa Firfir Key Wet(የደረቅ ዓሣ ፍርፍር ቀይ ወጥ)
Ingredients:
5 መካከለኛ ጭልፋ (ግማሽ ኪሎ ግራም) በደንብ ደርቆ በሙቀጫ የተወቀጠ የዓሣ ቋንጣ
1 መካከለኛ ጭልፋ (150 ግራም) በጣም የደቀቀ ቀይ ሽንኩርት
6 የሾርባ ማንኪያ (100 ሚሊ ሊትር) ዘይት
3 የሾርባ ማንኪያ አዋዜ
2 የሾርባ ማንኪያ ርጥብ ቅመም
1 የሻይ ማንኪያ ጥቁር ቅመም
ግማሽ የሻይ ማንኪያ ምጥን ሽንኩርት
3 የሾርባ ማንኪያ የተቀቀለ የአተር ክክ
1 የሻይ ማንኪያ ነጭ ቅመም
2 የሻይ ማንኪያ ጨው
Type:
Foods

Directions
1. ቀይ ሽንኩርቱን በራሱ ውሃው መጠጥ እስኪል ማብሰል፤
2. ምጥን ሽንኩርት ጨምሮ ማቁላላት፤
3. በደንብ እንደተቁላላ ዘይት በመጨመር ውሃ መጦ ሽንኩርቱና ዘይቱ ብቻ እስኪቀር መጠበቅ፤
4. አዋዜ ጨምሮ እንዳያር ሙቅ ውሃ ጠብ እያደረጉ ማብሰል፤
5. ትንሽ ውሃ ጨምሮ እንዲፈላ መተው፤
6. የአተሩን ክክ ጨምሮ እንዲበስል መተው፤
7. ርጥብ ቅመምና ጥቁር ቅመም መጨመር፤
8. አተር ክኩ ከሽንኩርቱ ጋር ተመሳስሎ በደንብ ሲበስል ትንሽ መረቅ እንዲኖረው በማድረግ እንዲፈላ መተው፤
9. ሲፈላ የተወቀጠውን የዓሣ ቋንጣ ላዩ ላይ እንደ ሽሮ መነስነስ፤
10. ፍርፍር ሲል ነጭ ቅመሙንና ጨውን አስተካክሎ ማውጣትና ለገበታ ማቅረብ፡፡