Yecheguara Wet (የጨጓራ ወጥ)

Ingredients:

ሩብ ኪሎ ተልጦ በቁመቱ የተቆራረጠ የበሬ ጨጓራ
6 መካከለኛ ጭልፋ (600 ግራም) ተልጦ በቁመቱ የተቆራረጠ ካሮት
3 መካከለኛ ጭልፋ (300 ግራም በቁመቱ የተቆራረጠ ፎሶሊያ
6 መካከለኛ ጭልፋ (600 ግራም) በቁመቱ የተቆራረጠ ቀይ ሽንኩርት
3 የሾርባ ማንኪያ ቅቤ
3 የሾርባ ማንኪያ ርጥብ ቅመም
6 የሾርባ ማንኪያ (00 ሚሊ ሊትር) በጠጅ ወይም በውሃ የተበጠበጠ ርጥብ ቅመም
1 የሻይ ማንኪያ ምጥን ሽንኩርት
1 የሾርባ ማንኪያ አዋዜ
1 የሻይ ማንኪያ ጥቁር ቅመም
1 የሻይ ማንኪያ መከለሻ
ሩብ ሊትር ዘይት
1 የሻይ ማንኪያ ጨው
Type:
Foods

Directions

1.ቀይ ሽንኩርቱን በሙቅ ውሃ ማብሰል፤
2.ምጥን ሽንኩርት ጨምሮ በደንብ ማቁላላት፤
3.ሽንኩርቱ ሲበስል አዋዜውን መጨመር፤
4.አዋዜው በደንብ ከተቁላላ በኋላ የተዘጋጀውን (ማለትም በፈላ ውሃ የተላጠውን) ጨጓራ መጨመር፤
5. በደንብ እንዲበስል አልፎ አልፎ እያማሰሉ መቆየት፤
6.ሲበስል ፎሶሊያውንና ካሮቱን በዘይት ለብቻ ጠብሶ ጨምሮ ትንሽ ማንተክተክ፤
7.ርጥብ ቅመምና ቅቤ ጨምሮ በደንብ ማብሰል፤
8.ጥቁር ቅመም ጨምሮ ማስተካከል፤
9.በጠጅ ወይም በውሃ የተበጠበጠ ርጥብ ቅመም ጨምሮ ማንሰክሰክ፤
10.ጨውና መከለሻ አስተካክሎ ማውጣትና ለገበታ ማቅረብ፡፡

Directions Video

amAmharic