Yebera Key Minchet Abish (የበሬ ቀይ ምንቸት አብሽ)

Ingredients:

ግማሽ ኪሎ ግራም የተፈጨ ቀይ ሥጋ
2 መካከለና ጭልፋ (300 ግራም) የደቀቀ ቀይ ሽንኩርት
5 የሾርባ ማንኪያ አዋዜ
2 የሾርባ ማንኪያ ርጥብ ቅመም
4 የሾርባ ማንኪያ ቅቤ
6 የሾርባ ማንኪያ (100 ሚሊ ሊትር) በጠጅ ወይም በውሃ የተበጠበጠ ርጥብ ቅመም
ግማሽ የሻይ ማንኪያ ምጥን ሽንኩርት
2 የሻይ ማንኪያ መከለሻ
1 የሻይ ማንኪያ ጨው
3 የሾርባ ማንኪያ ዘይት
Type:
Foods

Directions

1.ቀይ ሽንኩርቱን ሙቅ ውሃ ጠብ እያደረጉ ማብሰል፤
2. ምጥን ሽንኩርት ጨምሮ ማቁላላት፤
3.ዘይት መጨመርና እንዳያር ተጠንቅቆ ማቁላላት፤
4. አዋዜውን ቀጠን አድርጎ በጥብጦ መጨመር፤
5.በደንብ ከተቁላላ በኋላ ሥጋው ንጹህ ከሆነ ሳይታጠብ፤ ንፁህ ካልሆነ ግን የሥጋው ጣዕም እንዳይጠፋ በጠቅጣቃ ወንፊት ለቅለቅ አድርጎ ጨምቆ መጨመር፤
6. የስጋው ውሃ እስኪመጥ ከቁሌቱ ጋር በደንብ ማሸት፤
7.ርጥብ ቅመምና ቅቤ ጨምሮ እዲበስል ሙቅ ውሃ ሳያበዙ መተው፤
8.ሲበስል እሳት ሳያበዙ ማንተክተክና ጨው መጨመር፤
9.በጠጅ ወይም በውሃ የተበጠበጠውን ርጥብ ቅመም ከጨመሩና መከለሻ ካከሉ በኋላ ለ10 ደቃቂ ያህል ቀዝቀዝ ባለ እሳት አረፋ እስኪከት (አረፋው እስኪጠፋ) አንተክትኮ ማውጣት፡፡
ማስታወሻ
ለምንቸት አብሽ መሥሪያት የሚፈጨው ሥጋ ቀይ መሆን አለበት፡፡ ልፋጭና ስብ የበዛበት መሆን የለበትም፡፡ ስጋውን በንፁህ አስፈጭቶ ሳይታጠብ መጨመርም ይመረጣል፡፡ ምክንያቱም ደቆ የተፈጨ ስጋን ማጠብ የስጋውን ጣዕም ያጠፋዋል፡፡

Directions Video

amAmharic