Yebeg Zigin Wet(የበግ ዝግን ወጥ)
Ingredients:
ግማሽ ኪሎ ግራም በመካከለኛ መጠን የተከተፈ የሽንጥ ሥጋ
2 መካከለኛ ጭልፋ (300 ግራም) በደቃቁ የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት
2 የሾርባ ማንኪያ ለጋ ቅቤ
2 የሾርባ ማንኪያ በደቃቁ የተከተፈ ነጭ ሽንኩርት
2 ፍሬው ወጥቶ የተገረደፈ ቃርያ
3 የሾርባ ማንኪያ አዋዜ
1 የሾርባ ማንኪያ ዘይት
1 የሻይ ማንኪያ ጥቁር ቅመም
1 የሻይ ማንኪያ ጨው
Type:
Foods

Directions
1. ቀይ ሽንኩርቱን በውሃ ብቻ ማብሰል፤
2.ሽንኩርቱ ሲበስል ወዝ እንዲኖረው ዘይት መጨመር፤
3.ትንሽ ካቁላሉ በኋላ አዋዜውን መጨመር፤
4.አዋዜውን ሙቅ ውሃ ጠብ እያደረጉ ለትንሽ ጊዜ ማማሰል፤
5.ነጭ ሽንኩርቱን መጨመርና ሙቅ ውሃ ጠብ እያደረጉ ማዋሀድ፤
6. በደንብ ሲዋሀድ ጥቁር ቅመምና ቅቤ ጨምሮ በደንብ ማብሰል፤
7.ሲበስል ጨውን አስተካክሎ ቁሌቱን ማውጣት፤
8.ከወጣ በኋላ ለገበታ ሲቀርብ ስጋውን ከቁሌቱ ጋር እየለወሱ ቃርያ ጣል፣ ጣል አድርጎ ማቅረብ፡፡