Yeasa Shorba (የዓሣ ሾርባ)

Ingredients:

5 መካከለኛ ጭልፋ (ግማሽ ኪሎ ግራም) ፀድቶ በሎሚ የተለወሰ የተገረደፈ ዓሣ
2 መካከለኛ ጭልፋ (200 ግራም) የተገረደፈ ቀይ ሽንኩርት
1 መካከለኛ ጭልፋ (100 ግራም) የተገረደፈ ባሮ ሽንኩርት
4 የሾርባ ማንኪያ የደቀቀ ነጭ ሽንኩርት
2 የሾርባ ማንኪያ የደቀቀ ዝንጅብል
1 የቡና ስኒ (100 ግራም) ድፍን ምስር
4 ቃርያ
2 የሻይ ማንኪያ ጨው
የ ሎሚ ጭማቂ (መለወሻ)
Type:
Foods

Directions

1. ምስሩን በደንብ መጣድ፤
2. እንዲበስል ውሃ ጨምሮ መተው፤
3. ግማሽ ብስል ሲሆን ቀይ ሽንኩርት፣ ባሮ ሽንኩትና ዝንጅብል መጨመር
4. ሳይበዛ በመጠኑ ውሃ ጨምሮ እንዲፈላ መተው፤
5. ሲፈላ አረፋውን ከላይ እየገፈፉ ማንሳት፤
6. ምስሩና ሽንኩርቱ መብሰሉ ሲረጋገጥ ዓሣውን ጨምሮ ማንተክተክ፤
7. ነጭ ሽንኩርት መጨመርና እሳቱን ዝቅ አድርጎ አንሰክስኮ ጨው መጨመር፤
8. በቂ መረቅ እንዲኖረው አስተካክሎ ድፍኑን ቃርያ ጨምሮ ማውጣት፤
9. ለገበታ ሲቀርብ ቃርያውን አውጥቶ ማቅረብ፡፡

Directions Video

amAmharic