Yebera Zilzil Alicha Fitfit(የበሬ ዝልዝል አልጫ ፍትፍት)

Ingredients:

ግማሽ ኪሎ ግራም በትናንሹ የተዘለዘለ የታላቅ ወይም የሽንጥ ሥጋ
3 መካከለኛ ጭልፋ (300 ግራም) የተገረደፈ ቀይ ሽንኩርት
3 የሾርባ ማንኪያ ርጥብ ቅመም
4 የሾርባ ማንኪያ ቅቤ
1 የሻይ ማንኪያ ነጭ ቅመም
2 የሻይ ማንኪያ እርድ
5 ፍሬው ወጥቶ የተሰነጠቀ ቃርያ
1 የሻይ ማንኪያ ጨው
Type:
Foods

Directions

1.ቀይ ሽንኩርቱን በውሃ ብቻ ማብሰል፤
2.ሥጋውን ለብቻ ጥሩ አድርጎ ካጠቡ በኋላ መጨመርና በዝግታ ማሸት፤
3.ትንሽ ውሃ ጨምሮ እንዲበስል መተውና አልፎ አልፎ ማማሰል
4.ርጥብ ቅመሙን መጨመር፤
5.በደንብ ከተዋሀደ በኋላ እርድና ቅቤ መጨመር፤
6.ሥጋው እንዳይበጣጠስ እየጠበቁ ማብሰልና ነጭ ቅመም ጨምሮ ጨውን ማስተካከል፤
7. ሲስተካከል ቃርያውን ጣል፤ ጣል አድርጎና ፈትፍቶ ማውጣት፡፡

Directions Video

amAmharic