YeEnkulala Kikil Bemisir(የእንቁላል ቅቅል በምስር)

Ingredients:

5 የተቀቀለ እንቁላል
2 የቡና ስኒ (200 ግራም) በሙቅ ውሃ ለግማሽ ሰዓት የተዘፈዘፈ የምስር ክክ
2 መካከለኛ ጭልፋ (300 ግራም) የደቀቀ ቀይ ሽንኩርት
3 የሾርባ ማንኪያ አዋዜ
2 የሾርባ ማንኪያ ርጥብ ቅመም
1 የሾርባ ማንኪያ ምጥን ሽሮ
ግማሽ የሻይ ማንኪያ ምጥን ሽንኩርት
6 የሾርባ ማንኪያ (00 ሚሊ ሊትር) ዘይት
1 እግር ርጥብ በሶብላ
1 የሻይ ማንኪያ መከለሻ
1 የሻይ ማንኪያ ጨው
6 የሾርባ ማንኪያ (00 ሚሊ ሊትር) በጠጅ ወይም በውሃ የተበጠበጠ ርጥብ ቅመም
Type:
Foods

Directions

1. ቀይ ሽንኩርቱን በውሃ ብቻ ማቁላላት፤
2. ምጥን ሽንኩርቱን ጨምሮ ማቁላላት፤
3. ውሃው ሲመጥ ትንሽ ውሃ እደረጉ ማማሰል፤
4. ዘይት መጨመር፤
5. ዘይቱና ሽንኩርቱ ብቻ እስኪቀር ማማሰል፤
6. አዋዜ ጨምሮ ማሸት፤
7. ውሃው ሲመጥ አዋዜው እንዳያር ሙቅ ውሃ ጠብ እያደረጉ ማማሰል፤
8. ርጥብ ቅመም ጨምሮ ትንሽ ማንተከተክ፤
9. ምስሩን ጨምሮ ማብሰልና ሽሮውን ጨምሮ ማንተክተክ፤
10. ምስሩ ሲበስል በጠጅ ወይም በውሃ የተበጠበጠውን ርጥብ ቅመም መጨመር፣
11. መከለሻና ጨውን አስተካክሎ በሶብላ ጨምሮ ማውጣት፤
12. እንቁላሉን በሹካ ወጋ፣ ወጋ አድርጎ መጨመርና ለገበታ ማቅረብ፡፡

Directions Video

en_USEnglish